እኛን በተመለከተ

Asylum Help (የጥገኝነት ድጋፍ) ማነው?

Asylum Help በመላው ዩናይትድ ኪንግደም (UK) ለሚገኙ የጥገኝነት አመልካቾች ነጻ ምክርና አመራር የሚሰጥ ድርጅት የሆነው የMigrant Help አንድ አካል ነው። Migrant Help እ.አ.አ ከ1963 ጀምሮ ዩናይትድ ኪንግደም (UK) ውስጥ ለሚገኙ ስደተኞች የድጋፍ አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ የሚገኝ የዩናይትድ ኪንግደም (UK) የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው። ስለ Migrant Help (የስደተኞች ድጋፍ) ተጨማሪ መረጃዎችን ማግኘት ከፈለጉ እዚህ ላይ ጠቅ ያድርጉ።
asylum help team

Asylum Help የጥገኝነት አቤቱታ ሂደት እጅግ በጣም ውስብስብና አስቸጋሪ ሊሆን እንደሚችል ይረዳል። ወደ ዩናይትድ ኪንግደም (UK) አዲስ የመጡ ወይም ከመጡ ጥቂት ጊዜ ብቻ የቆዩ ሰው ከሆኑ Asylum Help (የጥገኝነት ድጋፍ) በዚህ ሂደት ውስጥ እርስዎን ለመደገፍ፣ ለመርዳትና በሂደቱ ለመምራት ዝግጁ ነው።

Asylum Help በመላው ዩናይትድ ኪንግደም (UK) የሚንቀሳቀስና ሚስጥርነቱ የተጠበቀና ከአድልዎ ነጻ የሆነ የምክር አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት ነው። የሚገኙበትን ሁኔታ በአግባቡ እንዲረዱና መረጃና እውቀት ላይ የተመሰረቱ ውሳኔዎችን እንዲወስኑ የሚያግዙ መረጃዎችንና አስፈላጊ ነገሮችን እንሰጣችኋለን። ማንኛውም ዓይነት የህግ ምክርና የጥብቅና አገልግሎትን መስጠት አንችልም፤ ቢሆንም ግን ተገቢ ሆኖ ሲገኝ በአካባቢዎ የድጋፍ አገልግሎቶችን ወደሚሰጡ ድርጅቶች እንመራዎታለን።

Asylum Help የጥገኝነት ጥያቄ ላቀረበ ወይም ዩናይትድ ኪንግደም (UK) ውስጥ የጥገኝነት ማመልከቻ የሚቀርበው የት እንደሆነ ለማወቅ ለሚፈልግ ማንኛውም ሰው የድጋፍ አገልግሎት የሚሰጥ መስሪያ ቤት ነው።

መብቶችንና እገዛዎችን የሚመለከት ምክር ልንሰጥዎ እንደምንችል ነገር ግን የህግ ምክር ወይም የጥብቅና አገልግሎት ልንሰጥዎት እንደማንችል እባክዎ ይወቁ። ልንረዳዎት የማንችል ከሆንን ደግሞ የሞያውን መስፈርቶች የሚያሟሉ ወይም ብቁ የሆኑ የህግ ባለሙያዎችን ዝርዝር እንሰጥዎታለን።