አገልግሎቶቻችን

Asylum Advice UK

Asylum Help (የጥገኝነት ድጋፍ) በመላው ዩናይትድ ኪንግደም (UK) ለሚገኙ አዋቂ የጥገኝነት አመልካቾችና ለእነሱ ጥገኞች በሚረዳቸው ቋንቋ ሚስጥርነቱ የተጠበቀና ከአድልዎ ነጻ የሆነ የምክር አገልግሎትና መረጃዎችን ይሰጣል።

Asylum Advice UK ዩናይትድ ኪንግደም (UK) ውስጥ ያለ የጥገኝነት ሂደትን የሚመለከት መረጃና ምክር ይሰጣል። Asylum Advice UK ቡድኖቻችን በሚከተሉት ጉዳዮች ዙሪያ ምክር ሊሰጧችሁ ይችላሉ፡-

 • የጥገኝነት ጥያቄን እንዴት እንደሚያቀርቡ
 • የገንዘብ ድጋፍ
 • የህግ አማካሪን ማፈላለግ
 • የጥገኝነት አቤቱታ ሂደት
 • የጤና አገልግሎት ማግኘት
 • የመኖሪያ ቤት ድጋፍ
 • ሌሎች የጥገኝነት ጉዳዮች
woman interviewing man

እንዴት ልንረዳዎት እንችላለን?

 • የዩናይትድ ኪንግደም (UK) የጥገኝነት ሂደትን ወይም የድጋፍ መብቶችን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ከፈለጉ በተለያዩ ቋንቋዎች የጥገኝነት ምክር መረጃዎች የሚገኙባቸው ገጾችን እዚህ ያግኙ
 • አዲስ ለመጡ የጥገኝነት ጠያቂዎች በመቀበያ ሳይቶች ላይ የገጽ ለገጽ የምክር አገልግሎት እንሰጣለን
 • ዩናይትድ ኪንግደም (UK) ውስጥ ከማንኛውም ቦታ Asylum Advice Helpline (Advice) አማካኝነት በቋንቋዎ በስልክ ምክር እንሰጣለን። የሚደውሉባቸው ስልክ ቁጥሮች ከታች ተቀምጠዋል።
 • ያሉበት አካባቢ በስልክ ወይም በአካል በመገናኘት ጠቃሚ አገልግሎቶችን ማግኘት እንዲችሉ እናደርጋለን። አስፈላጊ ሲሆንም የአውትሪች አገልግሎቶችን እንሰጣለን (ለጥቃት ተጋላጭ ለሆኑ ተገልጋዮች፣ የቡድን ውይይቶች ወይም ልዩ ጥያቄ ሲቀርብ)

የህግ ምክር ወይም የጥብቅና አገልግሎት ልንሰጥዎት እንደማንችል፤ አስፈላጊ ከሆነም አግባብነት ወዳለው ድጋፍ ሰጪ ድርጅት እንደምንመራዎት ይወቁ።

መብቶችንና እገዛዎችን የሚመለከት ምክር ልንሰጥዎ የምንችል መሆናችንን ነገር ግን የህግ ምክር ወይም የጥብቅና አገልግሎት ልንሰጥዎት እንደማንችል እባክዎ ይወቁ። ልንረዳዎት የማንችል ከሆንንም የሞያውን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ወይም ብቁ የሆኑ የህግ ባለሙያዎችን ዝርዝር እንሰጥዎታለን።